መነሻዎ አዲስ አበባ ነው እንበል። የተጠቀሙት ደሞ የግልዎን መኪና ወይም ተኮናትረው ሳይሆን በህዝብ ማመላለሻ መኪና ነው መሄድ የፈለጉት። ከአዲስ አበባ መቀሌ ከተማ ድረስ የሰላም ባስ በ460 ብር ይወስድዎታል። መነሻው ደሞ መስቀል አደባባይ። የቲኬት ቤሮአቸውም እሻው ከSquare Garden Cafe ጎን ነው። እስካኒያ አውቶብሶች ደሞ ከላምበረት አውቶብስ ተራ ይነሳሉ። 220ብር እስከ መቀሌ ድረስ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።
የሰላም ባስ ዘመናዊውን የYutong Bus ስለሚጠቀሙ ምቾቱ ከእሳኒያዎቹ ጋር ሲነጻጸር የትየለሌ ነው። ከምቾቱም በተጨማሪ የታሸገ ውሃ እና ቁርስ (ብስኩቶችን) ይጋበዛሉ። እኛ የተሳፈርንበት አውቶብሱ አየር ማቀዝቀዣው የማይሰራ ስለነበር በሙቀት ተሰቃይተናል። ሌላው የሰአት ልዩነታቸው ነው። ሰላም ባስ በ12 ሰዓታት ውስጥ መቀሌ ይገባል። እስካኒያዎቹ ግን እንደ ገበያው ነው። ቀጥታ ሰው ከሞላለት ይገባል ሰው ካጣ ደሞ መንገድ ላይም ሊጎልቶት ይችላል። በቂ ፍራንክ ካላገኙ መስሚያ የላቸውም።
እናም ሰላም ባስን ከአዲስ አበባ ይዘው ተነስተዋል እንበል (ማስታወቂያ መሰለብኝ መሰለኝ! ማርያምን! ምንም አልተከፈለኝም)። በ12 ሰዓታት ውስጥ መቀሌ ይከትማሉ። መቀሌ ውስጥ የሆቴልም ሆነ የፔንሲዮን ችግር ፈጽሞ አይታሰብም። ከ50 ብር ጀምሮ እንደልብ ያገኛሉ። እዛው የሰላም ባስ ማቆሚያ ላይ ሂቲ ሆቴልን ያገኛሉ። ሆቴሉ ባለ ሶስት ኮከብ ሳይሆን አይቀርም (የራሴ ግምት ነው)። አልጋ ለአንድ አዳር ከ225 ብር ጀምሮ እስከ 500 ብር ድረስ ያከራያሉ። እኔ የተከራየሁት የ225ቱን ነበር። የክፍሉ ጽዳት ጥሩ ነው። የራሱ የቁም ሻወር፣ መጸዳጃ ቤት፣ ልብስዎን ማስቀመጫ ቁም ሳጥን እንዲሁም ትንሽ የምትቆለፍ ኮመዲኖ አለው። የዚህ ክፍል ችግር የውሃ እጥረት ነው (ለነገሩ የውሃ ችግር የሃገሪቱ ባጠቃላይ ነው)። ቢሆንስ?! ታንከር ያዘጋጁዋ! ያበሳጫል! Toilet Flash ማድረጊያ ውሃ እንኳን ችግር ነበር። በባሊ እንደ Reserve የተቀመጠ ውሃ ስለነበር እንደምንም ተወጣነው እንጂ። ለሻወሩ ሙቅ ውሃ ከፈለጉ ግን ይተዉት! ከፈለጉ ሆቴል ይቀይሩ ወይም ሰፋ ያለ ኪስ ያለው ሱሪ ለብሰው ይሂዱ። ገንዘብዎን ይጭነቀው! ሙቅ ሻወር ምን ያደርጋል?! በቀዝቃዛ ታጥበው ጥቅልል ብለው አይተኙም! ብለን እንቀልዳ!
ወደ ጨዋታችን እንመለስ። መቀሌ ደረሱ። ሆቴል አልጋ አገኙ። አደሩ። ነጋ። አሁን ጉዞ መጀመርዎት ነው። በሉ ይነሱ! እዛው መቀሌ ውስጥ የአብርሃ ካስል እና የሰማእታት ሃውልት (ሃውልቲ) ብቻ ናቸው የሚጎበኙት (ከተለያዩ ሰዎች እንደተረዳሁት)። እኔና ጓደኛዬ ጊዜ ስላልነበረን በይደር አቆትተን ወደ መናሃሪያ ተጉዘናል።
አካሄዳችን ወደ ውቅሮ አይደል? ስለዚህ የ5 ብር ባጃጅ (ለአንድ ሰው) ተሳፍረን ወደ አውቶቢስ መናሃሪያ ተጉዘናል። እርስዎም ይህን እንዲያደርጉ እመክርዎታለሁ። እዚህ ላይ አንድ ነገር ልበልዎት። መቼም በጊዜና በሁኔታዎች አስገዳጅነት የማይቀየር የለም፣ ምናልባት ወደፊት ካልተበላሸ በቀር የመቀሌ ታክሲ ሹፌሮችም ሆኑ ረዳቶች እንዲሁም የባጃጅ ሹፌሮች በጣም ጨዋ፣ ሰው አክባሪ፣ አላግባብ ክፍያ የማያስከፍሉ ናቸው(በእርግጥ ይህን በራሱ ብዙ የሚባልለት የትግራይ ህዝብ መገለጫ ስለሆነ ወደፊት እመለስበታለሁ)። በተለያየ አጋጣሚ ይህንን ለማስተዋል ችያለሁና። አንድ ማሳያ ግን ልንገርዎት። ባጃጅ ወይም ታክሲ አስቆሙ እንበል።
እርስዎ: መናሃሪያ ስንት ትወስደኛለህ?
ሹፌር: 10 ብር
እርስዎ: ኧረ! 5 ብር አይደል እንዴ?
ሹፌር: አያዋጣኝም። ይልና በሩን ዘግቶት ይነካዋል።
ከተስማሙ ደሞ እዛው አድርስዎት የሚፈልጉትን መረጃ ይሰጥዎትና ይሄዳል። ታዲያ እርስዎ ፍራንኳ ላይ መሸወድ አለመሸወድዎን ለማወቅ ዞር ዞር ብለው መንገደኛን እስኪ ይጠይቁ። ራሱን ይነግርዎታል! የባጃጅ ሹፌሮቹ እኔን ተመችተውኛል! የአዲስ አበባ ላዳ ሹፌሮች ሰምታችኋል። ኧረ የሚኒባስ ረዳቶችም ብትሆኑስ! አሁን አሁንማ ሚኒባስ ውስጥ “ስንት ነው?” ብሎ መጠየቅ የመሸወጃ ምርጥ አጋጣሚ እየሆነ ነው። ነፍሴ ኮስተር ብሎ የ2.50 ሳንቲም መንገድን 5ብር ይልሃል። እሱ ጣጣ አለው እንዴ!
ወደ ጉዞአችን!
መናሃሪያ ደርሰዋል አሁን። የዉቅሮ ሚኒባሶችና ሎንቺናዎች በደንብ ያገኛሉ። በሎንቺና 15ብር ይከፍላሉ በሚኒባስ 20ብር ከፍለው ከ1 ሰዓት ያልበለጠ መንገድ ተጉዘው ውቅሮ ይገባሉ። “እንኳን ደህና መጡ!” የሚሏችሁ የውቅሮ ወጣቶች በትልልቅ ፌስታል የገብስ ቆሎአቸውን በአንድ እጃቸው ይዘው በሌላ እጃቸው እያውለበለቡ ይቀበሉዎታል። የቆሎ አድናቂ ከሆኑ በጆክ 10ብር ገዝተው አድናቂ ካልሆኑ ደሞ ተሳፋሪው ገዝቶ ሲበላ በሚፈጥረው የማላመጥ ድምጽና በቆሎ ሽታ ታጅበው መናሃሪያ ይደርሳሉ። ፓሲቭ እስሞከርን(Passive Smoker) ለሲጋራ ብቻ ማን ሰጠው? ለቆሎም ፓሲቭ ቺወር (Passive Chewer) አለዋ። ይሄ እንደውም ከባድ ነው ሆድ ያላውሳል።
አሁን ውቅሮ ንዎት! ነፍስ የሆነች ከተማ! ብዙ የጀበና ቡና ቤቶች፣ ብዙ ከረንቡላና ፑል ቤቶች፣ መጠነኛ ካፌዎች፣ ትንሽ መጠጥ ቤቶችና ሆቴሎች ያሉባት። ሲመሻሽ ወጣቱና ጎልማሳው በብዛት የጀበና ቡናቸውን እየኮመኮሙ በጨዋ ደንብ የሚያወጉባት። ውቅሮ ውስጥ ከጀበና ቡና መሸጫዎች ውጪ ለመጠጥ ቤቶች (ድራፍት፣ ቢራ ማለቴ ነው) ከቤት ውጪ (outdoor service) አላየሁም። እናም “በእዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ቡናን እንጂ ቢራን በህዝብ ፊት መጠጣት ነውር ነው” ብዬ ገመትኩ። ቡና ሻጮቹም ከመሃል ሃገር ወይም ከሌላ ቦታ የመጣን ተስተናጋጅ በፈገግታና በትህትና ቆንጆ ቡና የሚያስኮመኩሙባት። ውቅሮ! ይህንን ፍቅር የምትሰጥ ከተማ ውስጥ ነው ያሉት። አሁን ሆቴል ወይም አልጋ ፍለጋ መሄድ ይኖርብዎታል። ማደር ከፈለጉ ማለቴ ነው!
ውቅሮ ውስጥ አልጋ አይቸገሩም። ከተማዋ ትልቅ ናት። ትልልቅ መንግስታዊና ሃገር አቀፍ ስብሰባዎች ይካሄዱባታል። አልጋ እንደ መቀሌ ከ50ብር ጀምሮ ማግኘት ቢችሉም ደረጃቸው ግን ይለያያል። በ150ብር ንጹህ አልጋ፣ የግል መታጠቢያና መጸዳጃ ከሙቅ የገላ መታጠቢያ ውሃ ጋር በሽ በሽ ነው። ሙቅ ውሃው ይቅር ካሉ ደሞ በ80ብር ጸዳ ያለ ክፍል፣ የግል መታጠቢያና መጸዳጃ ጋር ያገኛሉ። ከዛማ ጓዞትን ክፍልዎት ውስጥ ጣል አድርገው ወደ ውቅሮ ጨርቆስ ቤ/ክ ጉብኝትዎ መጓዝ ነው። ተዘጋጁ?
ከሆቴልዎ ወጣ ብለው ውቅሮ ጨርቆስ (ቂርቆስ በትግርኛ ጨርቆስ ይሆን? ለማንኛውም “ቂርቆስ” እንዳይሉ! አለመግባባት ይፈጥራል) ብለው መንገደኛ ወይም ሊስትሮ ቢጠይቁ በቀላሉ አቅጣጫውን ይነገርዎታል። እንደውም ልጆች ከሆኑ እጅዎን ይዘው እዛው ቤተክርስቲያኑ በር ላይ ያደርስዎታል። ታዲያ እርስዎ የተባበረዎትን ልጅ እጁን በኪስዎ ማርጠብ ይኖርብዎታል። ለነገሩ አልኩ እንጂ እርስዎም ይሄ አይጠፋዎትም፣ ልጆቹም ቢሆኑ በ3ብር የሚያሳዩት ደስታ እርስዎን ፈገግ ያደርግዎታል።
እናም ወደ ቤተክርስቲያኑ ለመሄድ ዋናውን የተማዋን መንገድ ተከትለው ወይም የውስጥ ለውስጥ የኮብል እስቶን መንገዶችን ካጋመሱ በኋላ ወደ ውስጥ 200 ሜትር የእግር መንገድ ተጉዘው ቤ/ክርስቲያኑን ፊት ለፊትዎ ተራራ ላይ ጉብ ብሎ ያገኙታል። ተራራው በቁልቋልና በተለያዩ የበረሃ እጽዋትና ዛፎች የተሸፈነ ቢሆንም ቤተክርስቲያኑን ግን በርቀት ከመታየት ሊያግደው አልቻለም። ወደ ቤተክርስቲያኑ ማስገቢያው ዋና በር በዘመናዊ የብረት በር የታጠረ ሲሆን ወደ በሩ የሚያደርሰው ተራራማ መንገድ ደሞ በዘመናዊ መልክ የተሰራ በረዥም የደረጃዎችን ቅጥልጥል ተገንብቷል።
ውቅሮ ጨርቆስ ቤ/ክርስቲያን ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሰራ (ውቅር ቤተክርስቲያን ነው። ከተማዋም “ውቅሮ” የሚለውን ስም ከዚህ ሳይሆን አይቀርም ያገኘችው)። የቤተ መቅደሱ ከፍታ በግምት 20ሜትር ሲሆን ከውጪ እየዞሩ ለመጎብኘት የሚቻለው ¾ኛውን የቤተመቅደሱን ገጽታ ብቻ ነው። ¼ኛ የሚሆነው የቤተመቅደሱ አካል ከኋላ ካለው የተራራ አካል ጋር የተገናኘ ስለሆነ ዝግ ነው። ቤተመቅደሱ 4 በሮች ያሉት ሲሆን በፊት ለፊት ዋናው መግቢያ፣ ከላይ በስተግራ ሁለት በሮች፣ አንዱ ለካህናት መግቢያ ሌላው ደሞ የወንዶች መግቢያ ሲሆን በታች በስተቀኝ በኩል ደሞ የሴቶች መግቢያ በር አለው። እኛ እዚህ ቤተክርስቲያን የደረስንበት ሰአት ከምሽቱ 12:30 ስለሆነ መሽቶም ስለነበር አስከፍተን የቤተመቅደሱን የውስጥ ውበትና ክፍሎቹን መጎብኘት አልቻልንም። ቀደም ብሎ ለሚመጣ ጎብኝ ግን እዛው ግዚው ውስጥ የሚያስጎበኙ ካህናት ስላሉ በቀላሉ አግኝቶ ማነጋገር ይቻላል።
ስለቤተክርስቲያኑ አመሰራረት፣ መቼ እንደታነጸ፣ ማን እንዳነጸው፣ ምን ያህል ጊዜ እንደፈጀ ወዘተ ለማወቅ ጊዜውም ሁኔታውም ስላላገዙን ለማወቅና ለእርስዎ ለማካፈል አልቻልንም። ይቅርታም ይደረግልን እንላለን። ነገር ግን ይህቺ ትንሽ የጉዞ ማስታወሻ በመጠኑም ቢሆን ትጠቅምዎታለች ብዬ አስባለሁ። በተለይ ወደ ውቅሮ መጓዝ ከፈለጉ ሊጎበኟቸው ከሚገቡ ቦታዎች አንዱን በትንሹ ያስተዋቅዎት ይመስለኛል። ጥያቄ ካለዎት፣ ስለ ቦታው ተጨማሪ መረጃ ካለዎት፣ ወይም በጽሁፌ ውስጥ ስህተት ከሰራሁ በኢሜይል አድራሻዬ wemele4447@yahoo.com ብለው ይጻፉልኝ። ከስር በ comment መልክ መነጋገርም እንችላለን።
ሰላም ይቆየን

No comments:
Post a Comment