Friday, 8 March 2013

ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም” “አለመማረክ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም”


አቶ ዘነበወርቅ በላይነህ
 ይህ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛው መልካሙ ተክሌ  ከአባቴ ከአቶ ዘነበወርቅ በላይነህ ጋር ስለ ኮርያ ዘመቻው እና ስለጦርነቱ ያደረገው ቃለ መጠይቅ ነው። ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ እንደወረደ አቅርቤዋለው።

በአምስት ዙር ኮርያ ከዘመቱት 6037 ኢትዮጵያውያን መካከል 122ቱ በጦርነቱ ሞተዋል፡፡ አንዳቸውም አልተማረኩም ሳይማረኩ ግዳጃቸውን ፈጽመው ከተመለሱት  350ው የዛሬ 20 ዓመት የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበርን መስርተው ሰሞኑን የዘመቻውን 61ኛ ዓመት አክብረዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ከአስር አለቃ ዘነበወርቅ በላይነህ እና ከየኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር ፕሬዝደንት ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጓል፡፡