Thursday, 18 June 2015

የጉዞ ማስታወሻ 1(ዉቅሮ ጨርቆስ ቤ/ክርስቲያን)

መነሻዎ አዲስ አበባ ነው እንበል። የተጠቀሙት ደሞ የግልዎን መኪና ወይም ተኮናትረው ሳይሆን በህዝብ ማመላለሻ መኪና ነው መሄድ የፈለጉት። ከአዲስ አበባ መቀሌ ከተማ ድረስ የሰላም ባስ በ460 ብር ይወስድዎታል። መነሻው ደሞ መስቀል አደባባይ። የቲኬት ቤሮአቸውም እሻው ከSquare Garden Cafe ጎን ነው። እስካኒያ አውቶብሶች ደሞ ከላምበረት አውቶብስ ተራ ይነሳሉ። 220ብር እስከ መቀሌ ድረስ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።

የሰላም ባስ ዘመናዊውን የYutong Bus ስለሚጠቀሙ ምቾቱ ከእሳኒያዎቹ ጋር ሲነጻጸር የትየለሌ ነው። ከምቾቱም በተጨማሪ የታሸገ ውሃ እና ቁርስ (ብስኩቶችን) ይጋበዛሉ። እኛ የተሳፈርንበት አውቶብሱ አየር ማቀዝቀዣው የማይሰራ ስለነበር በሙቀት ተሰቃይተናል። ሌላው የሰአት ልዩነታቸው ነው። ሰላም ባስ በ12 ሰዓታት ውስጥ መቀሌ ይገባል። እስካኒያዎቹ ግን እንደ ገበያው ነው። ቀጥታ ሰው ከሞላለት ይገባል ሰው ካጣ ደሞ መንገድ ላይም ሊጎልቶት ይችላል። በቂ ፍራንክ ካላገኙ መስሚያ የላቸውም።